Skip to main content

Featured

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት ስብሰባ ተቀምጦ ነበር። በዚህም ም/ቤቱ በዩክሬን ጉዳይ የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ [የ193 አባል ሀገራት] አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ እንዲጠራ በድምፅ ወስኗል።

#BREAKING የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት ስብሰባ ተቀምጦ ነበር። በዚህም ም/ቤቱ በዩክሬን ጉዳይ የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ [የ193 አባል ሀገራት] አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ እንዲጠራ በድምፅ ወስኗል። ስብሰባው ዛሬ ሰኞ ይካሄዳል። ሩስያ ስትቃወም [ድምፅን በድምፅ የመሻር /veto power/ መብቷ እዚህ ላይ ተግባራዊ አይሆንም] ፤ ቻይና ፣ ህንድ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይህን አይነት ውሳኔ ሲወስን በ40 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በድርጅቱ ታሪክ ደግሞ 11ኛው መሆኑ ተነግሯል። #የደገፉ_ሀገራት ፦ 🇺🇸 አሜሪካ 🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም 🇫🇷 ፈረንሳይ 🇳🇴 ኖርዌይ 🇮🇪 አይርላድ 🇦🇱 አልባኒያ 🇬🇦 ጋቦን 🇲🇽 ሜክስኮ 🇧🇷 ብራዚል 🇬🇭 ጋና 🇰🇪 ኬንያ #የተቃወሙ ፦ 🇷🇺 ሩስያ #ድምፀ_ተአቅቦ_ያደረጉ ፦ 🇨🇳 ቻይና 🇮🇳 ሕንድ 🇦🇪 ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ (UAE)

የሩሲያ ወታደሮች ወደ ዋና ከተማ ኪዬቭ ተቃርበዋል ተባለ!


 የሩሲያ ወታደሮች ወደ ዋና ከተማ ኪዬቭ ተቃርበዋል ተባለ!


የሩሲያ አየር ወለዶች ከዩክሬን መዲና ኪዬቭ በ30 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ይገኛሉ።ከረፋድ ጀምሮ የሩሲያ አየር ወለዶች የዩክሬንን አንቶኖቭ ጦር ካምፕን በቁጥጥራቸው ስር አስገብተዋል።


በሌላ በኩል ደግሞ የዩክሬን ብሔራዊ ዘብ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ መጀመሩን አስታውቋል።በምድር፣ በአየርና በባሕር ሐሙስ ጠዋት በዩክሬን ላይ ጥቃት የከፈተችው ሩሲያ ከፍተኛ ውግዘት እየገጠማት ቢሆንም ዘመቻዋን ቀጥላለች።


የሩሲያ ጦር በተለያዩ አቅጣጫዎች ጥቃት የከፈተ ሲሆን ብረተ ለበስ ሜካናይዝድ ጦር ፈጣን ግስጋሴ እያደረገ ነው።በዚህም ከደቡብ አቅጣጫ በቤላሩስ ድንበር በኩል እንዲሁም በሰሜን ከክሬሚያ አቅጣጫ ወደ ዩክሬን አምርቷል።በኪዬቭ የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ፖል አደምስ ሩሲያ በቀጣይ ምን ልታደርግ እንደምትችል ግልጽ አይደለም ብሏል።


ምናልባት የአየር ኃይሉን ጦር ካምፕ የተቆጣጠሩት አየር ወለዶች ባሉበት ሆነው ሜካናይዝድ ጦሩን ሊጠብቁ እንደሚችሉ አመልክቷል።አልያም አየር ወለዶቹ የያዙትን የአየር ኃይል ካምፕ በኪዬቭ ላይ የአየር ጥቃት ለመክፈት ይጠቀሙበት ይሆናል ብሏል።

Comments