Search This Blog
We Africans are unique for our naturalness,way of life and beauty.I have a special interest in politics,economics and foreign relations in the Horn of africa 🐫 🌍 🐫 🌍 🐫 🌍 🐫 🌍🐫
Featured
- Get link
- X
- Other Apps
ሩስያ ፕሬዝዳንቱን ለመግደል አቅዳለች " - የዩክሬን ፕሬዝዳንት አማካሪ
" ሩስያ ፕሬዝዳንቱን ለመግደል አቅዳለች " - የዩክሬን ፕሬዝዳንት አማካሪ
የዩክሬን ፕሬዝዳንት አማካሪ ሚካሂሎ ፖዶሊያክ ሩስያ ኬያቭን ለመያዝ እና ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪን ለመግደል አቅዳለች ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪን አሁንም ድረስ በኪዬቭ እንደሚገኙ የገለፁት አማካሪው በዩክሬን ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪን በሰጡት መግለጫ " ባለን መረጃ ጠላት እኔን ቁጥር አንድ ኢላማ አድርጎኛል፤ ቤተሰቦቼን ደግሞ ቁጥር ሁለት ኢላማ አድርጓል። የሀገሪቱን መሪ በማጥፋት ዩክሬንን በፖለቲካ ማጥፋት ነው የሚፈልጉት ። የጠላት አጥፊ ቡድኖች ወደ ኪዬቭ መግባታቸውንም መረጃ አለን ነዋሪዎች ተጠንቀቁ የታወጀውንም ሰዓት እላፊ አክብሩ " ብለዋል።
ፕሬዜዳንቱ " እኔ በዋና ከተማዋ ነው የምቆየው፣ ቤተሰቦቼም ዩክሬን ናቸው። ልጆቼም ዩክሬን ናቸው። ቤተሰቦቼ ከዳተኞች አይደሉም የዩክሬን ዜጋ ናቸው " ሲሉም ተደምጠዋል።
ዩክሬን NATO እንዲደርስላትም እየተማፀነች ነው።
እስካሁን ድረስ ምዕራባውያኑ ኃያላን ሀገራት ማዕቀብ ከመጣል ባለፈ ወደ ዩክሬን ገብተው ከሩሲያ ጋር ውጊያ የመግጠም ሀሳብ ያላቸው አይመስልም፤ አሜሪካም ትላንት በፕሬዜዳንቷ ጆ ባይደን አማካኝነት ወታደሮቿን ከሩሲያ ጋር ለማዋጋት ወደ ዩክሬን እንደማታስገባ ማሳወቋ ይታወሳል።
አሁንም ጦርነት ቆሞ ለሰላም እድል እንዲሰጥ ጥሪዎች የቀጠሉ ሲሆን ሩስያ ውስጥም ጦርነቱን በመቃወም ሰልፎች እየተደረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ከዚህ ጋር በተያያዘም የታሰሩ ሰዎች በርካታ ናቸው።
@Hilinasolom
- Get link
- X
- Other Apps
Popular Posts
#The world must be well prepared for the next epidemic: WHO @Hilinasolom🇪🇹🇪🇹read more 👇
- Get link
- X
- Other Apps
#lets make Our environment free of garbage; #Let's cleanse ourselves from hatred ,Deputy Mayor Adanech Abebe🇪🇹🇪🇹H.W by @Hilinasolom
- Get link
- X
- Other Apps
Comments